በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ 20 አጥቢያ አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለጽሕፈት ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል።
በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት በኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመውና የተፈጸመው ዘግናኝና እጅግ አሳዛኝ ግድያዎች የኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችንን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በነጻነት የመኖርና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የመፈጸም መብትን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥታት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ መከታተልና የማያዳግም መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው እያሳሰብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትም የአካባቢው ችግር በመሰረቱ እስከሚፈታ ድረስ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።
በመጨረሻም በዚህ ዘግናኝና አሳዛኝ ግድያ ሕይወታቸውን
ላጡ ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ
መሆኑን እንገልጻለን
አባ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና
የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
