በአባያ ሐይቅ ላይ የእንቦጭ አረም እየተስፋፋ መሆኑና 304 ሄክታር የሐይቁን ክፍል መሸፈኑ ተገለጸ።
የሲዳማ ክልል አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ወርቁ ኡጌ፤ በተደረገ ግምገማ 304 ሄክታር የሐይቁ ክፍል በእንቦጭ አረም መጎዳቱ መረጋገጡን ገልጸዋል።
አረሙ በሐይቁ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ጠቁመው፤ ተገቢው ክትትልና እንክብካቤ ካልተደረገለት ጉዳቱ የበለጠ ሊባባስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የእንቦጭ አረሙን ለመቆጣጠርና የሐይቁን ሁኔታ ለመጠበቅ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።
እንቦጭ አረም የውሃ አካላትን በመሸፈን የፀሐይ ብርሃን ወደ ውሃው እንዳይደርስ የሚያደርግ ሲሆን፤ በውሃ ሥነ-ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።
