የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄ ነገር አይመለከታችሁም ወይ

Date:

ሴቷ ልጄ 13 ዓመቷ ነው። ትንሽ ዕድሜ ስትጨምር ቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እንደ ቀነኒ ስላለመሆኑ ምን ማስተማመኛ አለኝ? ይቺ ወጣት ልጅ ስላለፈችበት አስቸጋሪ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ የጥቃት መንገድ ብሎም ለሞት ስላበቃት ነገር ግልጽ ነገር አለማወቃችን ያለንበትን የደህንነት ደረጃ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱንም አመላካች ነው።

በግሌ በዚህ የፌስቡክ መንደራችን በከፍተኛ መብሰልሰል የዚችን አሳዛኝ ወጣት ፍትህ የማግኘት ጉዳይ እየወተወቱ የሚገኙት በብዛት ወንዶች መሆናቸውን ስላስተዋልኩ ለወደፊቱ ተስፋ እንዳልቆርጥ አድርጎኛል።

ከልቤ የማደንቃት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ያኔ ገና የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን የመሠረተች ሰሞን አበራሽ የምትባል የጠለፋ ወንጀል የተፈጸመባት እና አጓጉል ፍትህ የተሰጣትን የ14 ዓመት ታዳጊ እንዴት ፍትህ እንዳሰጠቻት እናስታውሳለን። እንደዚህ ዓይነት ጀግና ሴት የሕግ ባለሙያዎች (ማኅበሩን ጨምሮ) አሁን የት ናችሁ? አስጌ ከተባለው ድምፃዊ ዘለፋ በላይ ይሄ አያምም ወይ?

ፌስቡክ ተሳታፊ የሆናችሁም ያልሆናችሁም ወንድ የሕግ ባለሙያዎች የወንጀል ህጋችን ጥቃትን በተመለከተ ማንም ‘ይመለከተኛል’ የሚል ጥቃትን በተመለከተ በፈለገው ጊዜ ክስ መመስረት እንደሚችል አስቀምጦ የለ ወይ? ሰነዶች ሳይጠፉ ሰብሰብ ብላችሁ አትከሱልንም ወይ? ሴቶች ልጆች የሏችሁም ወይ?

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተለይ ስለሴቶች መብት የምትሟገቱ ዝምታችሁ ለራሳችሁ አላስፈራችሁም ወይ?

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄ ነገር አይመለከታችሁም ወይ?

በሰላም ወጥተን እንድንገባ ብቻ ሳይሆን በሰላም ማደራችንም ከፈጣሪ ቀጥሎ ደህንነታችንን በማስጠበቅ ቀን ከሌት የምትተጋው የጸጥታ ተቋም (ፖሊስ) ስለዚህ ጉዳይ ያልገባን ነገር ካለ እንዲብራራልን መጎትጎታችን ያስጠይቀናል ወይ?

ዋና ዋና የመገናኛ ብዙኃን ይህን እና መሠል ሴቶቻችን ላይ እስከ ሞት የሚያደርሱ ጥቃቶችን እያስተናገድን መምጣታችን እናንተን የማይመለከት ጉዳይ ነው ወይ?

እዚህ ጋ ስለአንዲት ነፍስ ቀነኒ እየተጠየቀ የሚመስላችሁ ካላችሁ በጣም ስታችኋል። የቀነኒ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት፣ ስቃዩዋ እና ሞቷ ብዙ ሴቶችን የሚወክል አንድ ምሣሌ እና ምልክት ነው።

ወደድንም ጠላንም ማኅበራዊ ሚዲያ አንድ ትልቅ መድረክ ሆኗል። ጩኸት ሲበረክት የሚመለከተው ሁሉ አድምጦ፣ መረጃ አሰባስቦ፣ አሰላስሎ፣ ገምግሞ እና የመፍትሔ እርምጃዎችን ወስዶ ለሕዝቡ ማሳወቅ አለበት። ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም አይባልም።

”Injustice anywhere is a threat to justice everywhere” Martin Luther King Jr.

Via: ሐውለት አህመድ (Phd) Hawlet Ahmed phd

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...