ሳዑዲ አረብያ ሁለት ኢትዮጵያውያን በሞት ቀጣች

Date:

ሳዑዲአረብያ ሁለት ኢትዮጵያውያንን ትናንት በሞት ቀጣች። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP የሳዑዲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ
እንደዘገበው ስማቸው የተገለጸው ሁለቱ የኢትዮጵያ ዜጎች በሞት የተቀጡት አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ተከሰው ነው።

በሳዑዲ አረብያየዜና አገልግሎት መግለጫ መሠረት ሁለቱም ሀሽሽ የተባለውን አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ጥፋተኛ ተብለው ነበር ። በዘገባው ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ክሱን አረጋግጦ በሰዎቹ ላይ የሞት ቅጣት መበየኑም ተጠቅሷል።

ሳዑዲ አረብያ ከዚህ ዓመት ጥር ወር አንስቶኢትዮጵያውያን ጨምሮ በሞት የቀጣቻቸው የውጭ ዜጎች ቁጥር ቢያንስ 101 ነው። ሀገሪቱ በአጠቃላይ በጎርጎሮሳዊው 2025 189 ሰዎችን በሞት ቀጥለች። ከመካከላቸው 88ቱ ዜጎቿ ናቸው።

ባለፈው በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. ቢያንስ 338 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል።በ2023 ደግሞ በሞት የተቀጡት ቁጥር 170 ነበር። በሳዑዲ አረብያ የሚፈጸመው የሞት ቅጣት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምንስቲ ኢንተርናሽናል በጥብቅ ተወግዟል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...