የህዝቦች ተቃውሞ በባንግላዲሽ

Date:

የባንግላዲሽ የአየር ሃይል ተዋጊ ጀት በዳካ ትምህርት ቤት ላይ ተከስክሶ 25 ተማሪዎችን ጨምሮ 31 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተጠያቂነትን እንዲሰፍን በባንግላዲሽ ሰልፍ ወተዋል።

የባንግላዲሽ ባለስልጣናት አደጋው የደረሰበትን ቦታ በጎበኙበት ወቅት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች እና ሌሎች በአቅራቢያው የሚገኙ ኮሌጆች ተማሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

በመዲናይቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች የፌደራል መንግስት ፅህፈት ቤት ሰብረው በመግባት የትምህርት አማካሪው ስልጣን እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተገልጿል፡፡

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ተማሪዎች የተገደሉት እና የተጎዱት ስማቸው እንዲገለጽ፣ ለቤተሰቦቻቸው ካሳ እንዲከፈላቸው፣ ያረጁ እና ለአደጋ የተጋለጡ ጄቶች እንዲቀየሩእና የአየር ሃይል ስልጠና አሰራር እንዲቀየር ጠይቀዋል።

ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ህዝቡን የበተነ ሲሆን በዚህም ወደ 80 የሚጠጉ ሠዎች መቁሰላቸውን የባንግላዲሽ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል።

በተቃውሞው መንግስት የሞቱትን እና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ስም በትክክል እንዲዘረዝር እየጠየቁ እንዲሁም ካሳ እና ህዝብ ይቅርታ እንደሚፈልግ እየተናገሩ ነው፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ 31 ሰዎች መሞታቸውንና 165 ሰዎች በከተማዋ በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል እየተደረገላችሀው እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ መሐመድ ዩኑስ እንዳስታወቀው አየር ኃይሉ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች አውሮፕላኖችን እንዳያሰማራ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...