ተንታ ወረዳ በናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

Date:


በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በተከሰተ የናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ የተንታ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  ወርቅነህ መላኩ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገለጸዋል።

በተንታ ወረዳ 01 ያመድ ቀበሌ ልዩ ሥሙ “ሳሬታ” በተባለ ቦታ ነሃሴ 10/2017 ዓ.ም ምሽት ላይ  በደረሰ የናዳ አደጋ  ምክንያት፤ የቤት እንሰሳትን ጨምሮ የአንድ አርሶ አደር ቤተሰብ አባላት ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።

በደረሰዉ የናዳ አደጋ ትልቅ ቋጥኝ የቆርቆሮ ክዳን ባለው መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ቤቱ ውስጥ የነበሩ አራት ሰዎች  የቤት እንሰሳት እንዲሁም ሣር ቤቱ በአደጋው እንደወደመም ኃላፊው አንስተዋል።

እስካሁን ከአደጋው አንድ አስከሬን ብቻ ማውጣት የተቻለ ሲሆን፤  የሌሎቹን 3 ሰዎች አስከሬን ለማውጣት የአካባቢው ማህበረሰብ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ቤቱ ላይ ያረፈው ቋጥኝ ድንጋይ ከባድ በመሆኑ አስከሬኖችን ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ አድርጎታልም ብለዋል ኃላፊው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...