ኢትዮጵያ 41ኛውን የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ከነሃሴ 19 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ “የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን ወደ ጥራት ትምህርት ማሻገር እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት” በሚል መርህ በአዲስ አባባ እንደሚከናወን ተገለፀ።
የማህበሩ አባል ሀገራት በትምህርት ምዘናና ፈተና ዙሪያ አዳዲስ ፈጠራዎችን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ እሳቤዎችና ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲሁም ልምዶችን መለዋወጥ እና ባለሙያዎች ሥልጠና የሚያገኙበት ምቹ ሆኔታ የሚፈጥር መሆኑ ነው የትምርህት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና የማህበሩ ምክትል ሊቀመንበር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ያስታወቁት፡፡
በአባል ሀገራቱ መካከል ትብብርን እና ትስስርን ለማጠናከር የትምህርት ምዘናና የፈተና ስራዎችን በጋራ የመስራት እና ሌሎች ጉዳዮች የጉባኤው ዓላማ መሆኑ ነው የተመላከተው።
በጉባኤው ከ30 በላይ ሀገራት የሚመጡ ከ500 በላይ ልኡካን እና በአፍካ የትምህርት ምዘና ካውንስል አመራሮች ባለሙያዎች ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ያሉ ተመራማሪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች የመንግስት ከፍተኛ የሥራ አመራሮችም ተሳታፊ ይሆናሉ።
በዚህም በአፍሪካ የጋራ የትምህርት ምዘና ማዕቀፍ ላይ ጉባዔው እንደሚመክር የገለጹት ሊቀመንበር፣ ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራትም በምርጥ ተሞክሮዎቻቸውና ቴክኖሎጂች የሚቀርቡበት ልምድ የሚቀያየሩበት መድረክ እንደሚሆነም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ 41ኛውን የትምህርት ምዘና ታስተናግዳለች
Date:
