የቀድሞው የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ተጠየቀ

Date:


እንደ ለ ፓሪዚያን ዘገባ ከሆነ፣ በነሐሴ 16  በኪንሻሳ የዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ወታደራዊ ፍርድ ቤት “በጦር ወንጀሎች”፣ “ክህደት” እና “አመፅን በማደራጀት” በሞት እንዲቀጡ ጠይቋል። በተጨማሪም “በሴራ” ወንጀል የ15 ዓመት እስራት እንዲቀጡም ጥያቄ ቀርቧል።

ለአመታት ከሀገር ውጭ የኖሩት ጆሴፍ ካቢላ በሌሉበት ነው ክሱ  የተመሰረተው። የዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤቱን የሚወክሉት ጄኔራል ሉሲየን ሬኔ ሊኩሊያ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከኤም23 ታጣቂ ቡድን ጋር ተባባሪ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ አቅርበዋል።

ይህ ክስ በኮንጎ ባለስልጣናት እና በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ያለውን ቀጣይ ውጥረት ያሳያል።

አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ዓይነቱ የቀድሞ የሀገር መሪ በሌለበት የሚካሄድ የፍርድ ሂደት በአፍሪካ እምብዛም የማይታይ ነው፣ ይህም ለፍርዱ ሂደት ጠንካራ ምሳሌያዊ ትርጉም ይሰጠዋል ብለዋል።

ከህጋዊ ጉዳዩ ባሻገር፣ ይህ ክስ ውስብስብ በሆነ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ እየተካሄደ ነው። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምሥራቃዊ ክልሏ ከፍተኛ የፀጥታ ችግሮች መጋፈጧን የቀጠለች ሲሆን ይህ የፍርድ ሂደት መንግሥት በታጣቂ ቡድኖች እና ሊሆኑ በሚችሉ ደጋፊዎቻቸው ላይ ያላቸውን ጥንካሬ ለማሳየት ያለውን ቁርጠኝነት ሊያጠናክር ይችላልም ተብሏል።

የካቢላ ጉዳይ የትጥቅ ግጭት ጠባሳው ጥልቅ በሆነበት ሀገር ውስጥ በፍትህ እና በፖለቲካዊ መረጋጋት መካከል ያለውን ሚዛን ለመጠበቅ ያለውን አስቸጋሪነትም ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...