ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ ሊጀመር ነው

Date:

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

በባለስልጣኑ የአየር ትራንስፖርትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ አቶ እንደሻው ይገዙ በ2018 ዓ.ም ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተጨማሪ በሌሎች የሃገሪቱ ክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ እንደሚጀመር ተናግረዋል።

በዚህም ባለስልጣኑ ከግል የበረራ ድርጅቶች ጋር በበረራ አገለልግሎት ዙሪያ እየተወያየ መሆኑ ተጠቁሟል።

አቶ እንደሻው ዓለም አቀፍ በረራዎቹ ለአብነትም በባህር ዳር፣ መቀሌ እና ድሬደዋ ቢደረጉ የሃገሪቱን የወጪ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ልማቱን የሚደግፍ እንደሆነ አንስተዋል።

በሌላ በኩል የክልል ኤርፖርቶችን ለማስተሳሰር መታቀዱን ገልጸው ይህም የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር እና የደንበኛውን እንግልት ለመቀነስ እንደሚያስችል አመላክተዋል።

ከሚዛን ቴፒ – ጅማ – ጋምቤላ – አሶሳ እንዲሁም ከድሬደዋ – ሃረር – ባሌሮቤ የተሳሰረ በረራ እንዲኖር ለማድረግ መታሰቡንም ገልፀዋል።

በተጨማሪም መንፈሳዊ ጉዞዎችን ከክልል ኤርፖርቶች ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸው የሃጂ ኡምራ ጉዞ፣ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ገናን በላሊበላ እና ጥምቀትን በጎንደር ጉዞዎችን ለማስተናገድ መታቀዱን ነው።

ኢፕድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...