ኢትዮጵያዊው ኃይለማሪያም ኪሮስና ሲፋን ሀሰን የሲዲኒ ማራቶንን አሸነፉ

Date:

ከ35ሺ በላይ ሠዎች በተሳተፉበት የ2025 TCL SYDNEY MARATHON በኤሊት አትሌቶች ኢትዮጵያዊው ኃይለማርያም ኪሮስና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን አሸናፊነታቸውን ሲያውጁ በውድድሩ ብዙ የተወራለት ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ዘጠነኛ በመሆን አጠናቋል።

ኃይለማርያም ኪሮስና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሠን ውድድሩን 2:06:06 እና 2:18:22 በሆነ ሠዓት በመግባት የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር አሸንፈዋል።

ከ2024 ጀምሮ ቦስተን፣ ቶኪዮ፣ በርሊን፣ ቺካጎ፣ ለንደንና ኒውዮርክ ሲቲ ቀጥሎ ወርልድ ሜጀር ማራቶን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቶ የተካሄደው የሲዲኒ ማራቶን በወንዶች የ28 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ኃይለማርያም ኪሮስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አዲሱ ጎቦና በ10 ሠከንዶች ዘግይቶ የቦታው ሪከርድ የሆነ 2:06:16 በማስመዝገብ በሁለተኛነት አጠናቋል።

በኤሊት ሴቶች አይበገሬዋ ሲፋን ሀሰን ታሪክ መስራቷን ባሳየችበት ውድድር በሲዲኒ ምድር ከ2:18:22 በታች በመግባት የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ሆና ተመዝግባለች።

የወቅቱ የአለም የማራቶን አሸናፈነቷንና በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊነቷን በማወጅ በሶስት ውድድር ሜዳሊስት በመሆን አዲስ ታሪክ ያፃፈችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንዳዊ ሲፋን ሀሰን የአለም አትሌቲክስ ክስተት መሆኗን በሲዲኒ ጎዳና ላይም አሳይታለች።

የአለማችን አስገራሚዋ አትሌት ሲፋን ሀሰን በአፕሪል ወር በለንደን ማራቶን 2:19:00 በመግባት በሶስተኝነት ካጠናቀቀች በኃላ ያስመዘገበችው የማራቶን የመጀመሪያ ድሏም ሆኗል።

በሴቶች ምድብ ሲፋን ሀሰንን ተከትላ ኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮስጊ በሁለተኝነት ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያዊያኖቹ ወርቅነሽ ኢዶሳና ኩሜሺ ሲቻላ ሶስተኛና አራተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

♦️የሲዲኒ ማራቶንን በማሸነፍና ሪከርድ በመስበር የሚገኝ ሽልማት

👉በወንድም በሴትም አንደኛ ለሚወጡ ለእያንዳንዳቸው 30ሺ ዶላር

👉በወንድም በሴትም ሁለተኛ ለሚወጡ ለእያንዳንዳቸው 20ሺ ዶላር

👉በወንድም በሴትም ሶስተኛ ለሚወጡ ለእያንዳንዳቸው 10ሺ ዶላር

👉በወንድም በሴትም አራተኛ ለሚወጡ ለእያንዳንዳቸው 5ሺ ዶላር

♦️የቦታውን ሪከርድ ለሚያሻሽሉ ደግሞ ተጨማሪ 10ሺ ዶላር

በወንድም በሴትም አምስተኛ ለሚወጡ ለእያንዳንዳቸው 2500ሺ ዶላር ያገኛሉ። አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሸናፊዎች 135ሺ የአውስትራሊያ ዶላር መድባለች።


Sydney Marathon 2025 ኤሊት ወንዶች ውጤቶች

ሀይለማሪያም ኪሮስ 🇪🇹 2:06:06 CR

አዲሱ ጎበና 🇪🇹 2:06:16

ቲቤሎ ራማኮንጎአና 🇱🇸 2:06:47

ሙስጠፋ ሆዳድ 🇲🇦 2:07:17

ኤድዋርድ ቼሴሬክ 🇰🇪 2:07:38

አራኦ ማሳቶ Arao (JPN) 2:07:42

ላባን ኮሪዮር 🇰🇪 2:08:06

ፍሊክስ ኪፕቱ 🇰🇪 2:08:18

ኤሊዩድ ኪፕቾጌ 🇰🇪 2:08:31

ቪክቶር ኪፕቺርቺር 🇰🇪 2:09:01

♦️ኤሊት ሴቶች ውጤቶች

ሲፋን ሀሠን (NLD) 2:18:22 CR

ብሪጅድ ኮስጌይ 🇰🇪 2:18:56

ወርቅነሽ ኢዴሳ 🇪🇹 2:22:15

ኩሜሺ ሲቻላ 🇪🇹 2:22:50

ኢቫሊን ቺርቺር 🇰🇪 2:23:13

ሆሶዳ አይ 👺 2:23:27

ሊኔ ፖምፒአኒ 🇦🇺 2:24:47

ጄሲካ ስቴንሠን 🇦🇺 2:28:56

ሊሳ ዌይትማን 🇦🇺 2:29:34

አቢጋሊ ኖርድበርግ 🇦🇺 2:35:43

በጋዜጠኛ ይስሀጠቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...