ህዳሴ ኢትዮጵያዊያን ላባቸውን እንደቀለም፣ ክንዳቸውን እንደብዕር አድርገው የጻፉት ደማቅ ታሪክ ነው

Date:

ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ላባቸውን እንደ ቀለም፤ ክንዳቸውን እንደ ብዕር አድርገው የጻፉት ደማቅ ታሪክ ነው ሲሉ የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

 
ኃላፊው እንደገለጹት፤ ህዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያዊያን በላብና ደማቸው የሰሩት የዚህ ትውልድ ዳግማዊ ዓድዋ ነው፡፡

ህዳሴ በትብብርና በመተሳሰብ እንዲሁም በመተማመን መሥራት የእድገት እና የይቻላል መሠረት ከመሆኑ ጎን ለጎን የስነ ሃሳብ ቤተ ተሞክሮ መሆን የሚችል እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

‹‹ህዳሴ የጋራ እሴት ልህቀት ማዕከል ነው›› ያሉት አረጋዊ (ዶ/ር)፤ የቁጠባ ባህል ከማስተማሩ በተጨማሪ ለሀገሪቱ የአሸናፊነትና የሉዓላዊነት ጸጋ አጎናጽፏል ብለዋል፡፡

ህዳሴ የአይቻልም ስሜትና የተለያዩ የቅኝ ግዛት ውሎች  የኮሰመኑበት መሆኑን ገልጸው፤ለግድቡ እውን መሆን ኢትዮጵያ ስትከተለው የነበረው የፍትሃዊነትና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው አስታውሰዋል፡፡

‹‹ግድቡ መላው ኢትዮጵያዊያን ድንበርና ርቀት ሳይገድባቸው ያቆሙት ምሶሶ ነው›› ያሉት አረጋዊ (ዶ/ር)፤ ይህም የዘመናት ቁጭትን የገረሰሰ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ለግድቡ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ አንስቶ እስከ አሁን 23 ነጥብ ስምንት ቢሊየን ብር በላይ ከህብረተሰቡ ተሰብስቧል ብለዋል፡፡

ግድቡ ለአፍሪካ ምሳሌ በመሆኑ ከዓድዋ ቀጥሎ የአንድነትና የሉዓላዊነት ሞዴልም ያስብለዋል፡፡

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...