ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ ምግቦች!

Date:

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአካሄደው የገበያ ዳሰሳ ጥናት የቁጥጥር መስፈርቱን ያላሟሉ የተለያዩ የምግብ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳስባል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንና ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአደረገው የገበያ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ተመርተው በገበያ ውስጥ አስገዳጅ የደረጃ ምልክት ሳይኖራቸዉ ወይም ሳይለጥፉ እንዲሁም አስገዳጅ የገላጭ ፅሁፍ ስታናድርድ CES 73 ሳያሞሉ ወደ ገበያ መውጣታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

መስፈርቱን ያላሟሉት የምግብ ምርቶች የገበታ ጨው፣ የለውዝ (የኦቾሎ) ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ አቼቶ፣ ከረሜላ እና ማር ሲሆኑ በምርቶቹ ላይ የተገኘው ጉድለት ደግሞ የማምረት የብቃት ማረጋገጫ (ሲኦሲ) የሌላቸው፣ የአምራች ድርጅት ስምና አድራሻ እንዲሁም አስገዳጅ የደረጃ ምልክት የሌላቸው፣ ምርቱ የተመረተበትና የሚያበቃበት በተለይም መለያ ቁጥር የሌለውና የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያለመገለፅ ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት የምግብ ምርቶች ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለሰልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

የገበታ #ጨው

  1. ሴፍ 16. ዜድ
  2. ማሚ 17. ማሂ
  3. ሶም 18. ኤልሳ
  4. ኒያ 19. አርኪ
  5. ኤ ኤም 20. ሜናታ
  6. አሜን 21. ፎር ኤፍ
  7. ኑና 22. ዋን
  8. ዘመን 23. አዮዲን
  9. ስኬት 24. ዳግም
  10. ቴንሲያ 25. ቶም
  11. እሙ 26. ጆይ
  12. ጠሊል 27. ሳሊህ
  13. መስቱራ 28. ዛክ
  14. ጊዜ 29. ትዝታ
  15. ኩል 30. ዊን

የለውዝ (ኦቾሎኒ) ቅቤ

  1. መና 8. ዓለም
  2. ፋና 9. ፀዬ (Tseyie)
  3. ሰናይት 10. አዱሊስ
  4. MAZA( ኤም ኤ ዜድ ኤ) 11. ጊፍት
  5. ሉሲ 12. ስዊት
  6. ኤ ኤፍ 13. ሐበሻ
  7. አያልነህ 14. ሀናን

የምግብ ዘይት

  1. ፍትህ 7.ዝናሽ
  2. የኛ 8. ፍፁም
  3. Tina Oil 9. ሙሐ
  4. ፋሚሊ 10. ተስኒም
  5. እድገት 11. ፀሐይ
  6. ረዲ 12. እፎይታ

አቼቶ

  1. Hade Aceto

ከረሜላ

  1. Hawi Fruits candy
  2. Best Jar
  3. MAMIE
  4. Mamie Lollipop
  5. Best Pop Lollipop ማር
  6. ፀደይ ማር
  7. ኬሪ የጫካ ማር
    (የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...