ትራምፕ ኒውዮርክ ታይምስን በ15 ቢሊየን ዶላር ሊከሱ ነው

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ስም በሚል በኒውዮርክ ታይምስ ላይ በ15 ቢሊየን ዶላር ክስ እንደሚመሰርቱ ተናገሩ።

“ኒው ዮርክ ታይምስ በነፃነት እንዲዋሽ፣ እንዲያደበዝዘኝ እና ስሜን እንዲያጠፋ ተፈቅዶለታል፣ እናም አሁን ያ ያቆማል” ሲሉ ትራምፕ የግል ንብረታቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ትሩዝ ሶሻል ላይ አጋርተዋል፡፡

ባለፈው 2024 ዓመት በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የካማላ ሃሪስን የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት የኒወዮርክ ታይምስ ድጋፍ “ለዲሞክራት ፓርቲ ቃል አቀባይ” ሆኗል ሲሉ ትራምፕ ገልጸዋል።

ትራምፕ ክሳቸውን የጀመሩት የሪፐብሊካን ጠንካራ ይዞታ በሆነችው ፍሎሪዳ ነው። ጋዜጣውን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነታቸው የማይመቹ የግራ ዘመም ሚዲያዎችን ቅር እንደተሰኘባቸው በክሳቸዉ ላይ ጠቁመዋል፡፡

ትራምፕ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣን ለመክሰስ ሲሞክሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።እ.ኤ.አ. በ 2023 አንድ ዳኛ በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ትራምፕ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርገውታል ፣ በክሱ ውስጥ ያሉት የይገባኛል ጥያቄዎች “እንደ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል ።

የ100 ሚሊዮን ዶላር ክስ ጋዜጣውን እና የትራምፕን የእህታቸዉን ልጅ ሜሪ ትራምፕን የግብር መዝገቦቹን ለማግኘት “በተንኮል ሴራ ተሰማርቷል” ሲሉ ከሰዋል።

ትራምፕ በ2023 ሌላ የስም ማጥፋት ክስ በሲኤንኤን ላይ ቢመሰርቱም ተሸንፈዋል፡፡ ሲኤንኤን ከአዶልፍ ሂትለር ጋር አመሳስሎኛል በሚል የመሰረቱት ክስ የ475 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም አንድ የፌደራል ዳኛ ክሱን ውድቅ አድርጎታል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...