የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ማጠናከሪያ የሚውል የ400 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ ድጋፍ የህዝብ መረጃ መግለጫ ሥርዓት ለመዘርጋት እና እንደ በአክሲዮን ልውውጥ መገበያየት የሚችሉ የኢንቨስትመንት ፈንድ አይነት (ETFs)፣ ሱኩክ (ከሸሪአ ጋር የተጣጣሙ የፋይናንስ መሳሪያዎች) እና አረንጓዴ ቦንዶች የመሳሰሉ አዳዲስ እና የተለያዩ ምርቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ነዉ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐና ተኸልኩ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የካፒታል ገበያ ልማት ማኔጀር አካኔ ዞክፖ በአዲስ አበባ በተደረገ ስነ-ስርዓት ላይ ስምምነቱን ፈርመዋል።
ይህ ድጋፍ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የፋይናንስ ዘርፉን ለማጠናከር ወሳኝ ነው ተብሏል።
CapitalNews
