ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ዓህመድ(ዶ/ር) የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ የነበሩትን እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አድርገው ሾሙ፡፡
ከሁለት ሳምንታት በፊት በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን በለቀቁት የኢትጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ቦታ ሰሞኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) መሾማቸው በማህበራዊ ድረገጾች ሲነገር ቢቆይም፣ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ተሾመዋል፡፡
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ በነበሩት ለገሰ ቱሉ(ደ/ር) ቦታም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን ወ/ሮ እናታለም መለስን፣ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አድርገው ሾመዋል።
