የኢትዮጵያን የኒውክለር ተጠቃሚነት እንደሚደግፍ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ አረጋገጠ

Date:

ኢትዮጵያ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ማረጋገጡን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒሰቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከመስከረም 15 እስከ 19 በኦስትሪያ፥ ቪየና እየተካሄደ ባለው 69ኛው የ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጄንሲ(IAEA) መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ራፋኤል ማርያኖ ግሮሲ ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በማሕበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያሰራጨው መረጃ የመላክታል።

ውይይቱ ኢትዮጵያ በምታካሂደው የሰላማዊ ኒዉክሌር ሃይል ፕሮግራም፣ በሰው ሃይል አቅም ግንባታ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን በዚህ ወቅት የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ራፋኤል ማርያኖ ግሮሲ ኤጄንሲው የኢትዮጵያን ሰላማዊ የኒውክለር ኃይል ተጠቃሚነት እንደሚደግፍ ለሚንስትሩ አረጋግጠዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒሰቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የሰላማዊ ኒውክሌር ኢነርጂ ፕሮግራሞችን እውን ለማድረግ መሠረት በመጣል ላይ መሆኗን እና ወደትግበራ ለመግባትም ሰፊ ጥረት እያደረገች መሆኗን ገልጸው ኢጀንሲው እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

➲ t.ly/SOXU

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...