ለቡርኪናፋሶ ካቦሬ በ64′ 81′ 90+6′ ደቂቃ በማግባት ሀትሪክ ሲሰራ ለኢትዮጵያ በስህተት የተገኘችውን ኳስ በ83ኛው ደቂቃ ቢኒያም አይተን አስቆጥሯል።
የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ተሻለው ሲባል መልሶ የሚታመም ቡድን ሆኗል።
ቡድኑ በሰርአት ኳስ ተቀባብሎና አደራጅቶ ተቃራኒ ቡድን ግብ ክልል ጋር መድረስ ተራራ ሆኖበት ታይቷል።
ተከላካዩ ከመሀል ክፍሉ ጋር የማይናበብ፣ መሀል ክፍሉ ለአጥቂዎች ኳስ የማይመገብ ተጋፍተው ኳስ መቀማት የከበዳቸው ፣ትንሽ ሲገፉ የሚወድቁ ተጫዋቾች ታይተዋል።
ከ 30 ዲግሪ ሴንት ግሬድ በላይ የነበረው ሙቀት ኳሱን ያከበደው ቢሆንም የኢትዮጵያ ኳስ “ሀ “ብሎ ከታች ከታዳጊዎች መጀመር እንዳለበት ጨዋታው ምስክር ነው።
ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን ረጅም ኳሶቹ ሁሉ የከሸፉ ነበሩ ፣ ያለ አግባብ ሰአት ሲያባክን ታይቷል።
በምሽቱ ጨዋታ ኳስ ሲቀማ እና የተለየ ተጋድሎ ሲያሳይ የነበረው የመሀል ተከላላዩ ራምኬል ጀምስ ነበር ።
በአንፃራዊነት ተከላካይ ክፍሉ የተሻለ ነበር ማለት ይሻላል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ግራ የገባው ቡድን ይዘው ነው ለአለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት።
ቡርኪና ፋሶን የገጠመው ዋልያ ከዚህ ጨዋታ ምን እንደሚፈልግ መረዳት ከባድ ነበር።
በቅጡ ረጅምም ሆነ አጭር ኳስ የማይቀባበል ፣በቅጡ የማያጠቃ ደካማ ቡድን ሆኖ ነበር የቀረበው።
