- ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከበቅሎ ቤት ወደ ፒያሳ ኑር መስጂድ ያመራል::
- ቀትር ዙሁር ሶላት ፒያሳ ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ይሰገዳል::
- ከሰዓት ሚሊኒየም አዳራሽ ሀገራዊ ሽኝት ይካሄዳል
- በመጨረሻ ቀብራቸው ጋርመንት በሚገኘውና ደረሶችን በሚያስተምሩበት ግቢያቸው በወሲያ (ኑዛዜያቸው) መሠረት ይፈፀማል::
እንዲህ ያሉ ታላላቅ ሰዎች ሲያልፉ ለጀናዛ (አስክሬን) ትጥበት ልብስ እንኳ አይወልቅም:: መጨረሻ በተለበሰው ልብስ ሳይወልቅ ታጥቦና ተከፍኖ ሥርዓተ ግብዓተ መሬት ይከናወናል::
ኃይማኖትና ብሔር ሳይለይ ለሁሉም ወዳጆቻቸው
- ፒያሳ የሚመቸው ቀትር ላይ ፒያሳ ሰፈር በኒን ኑር መስጂድ
- ለሀገራዊ ሽኝት 8 ሰዓት ሚሌኒየም አዳራሽ
- 10 ሰዓት ኃይሌ ጋርመንት አትክልት ተራ ዝቅ ብሎ ወይም ከአቃቂ ወደ ለቡ ሲኬድ ዳገቱ እንዳለቀ ድልድዩ ጋር መሰናበት ይችላል::
በሙፍቲ ዑመር ሀጅ ዑመር ኢድሪስ ሞት አንድነት እንደሰጠን ሀገራዊ አንድነት ይስጠን:: ሰላም ያምጣልን::