የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንበሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት ጥልቅ ኀዘኋን ገለጸች

Date:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ሙፍቲ የነበሩት ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት መራር ኀዘን እንደተሰማት ገለፀች።

ቤተክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በአባ ሳዊሮስ ስም ባወጣችው መግለጫ፣ የሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን የዕረፍት ዜና በታላቅ ሐዘን እንደተቀበለችው አስታውቃለች።

በመግለጫው እንደተገለጸው፣ የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በሕይወት ዘመናቸውና በአገልግሎት ቆይታቸው ለአገር አንድነትና ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጡ፣ የርህራሔ፣ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት የነበሩ ታላቅ አባት ነበሩ።

በተለይም፣ እርሳቸው በነበራቸው መልካም ስብዕና፣ ርኅራኄና ለሕዝባቸው በነበራቸው ፍቅር የተነሳ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ አክብሮትና ተወዳጅነትን ያተረፉ አባት እንደነበሩ ቤተክርስቲያኗ አስረድታለች። “በእኒህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት በነበሩት” በማለትም ቤተክርስቲያኗ ለሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ያላትን ክብር ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ ይህንን ጥልቅ ኀዘን ስትገልጽ፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእምነት አባቶችና ተከታዮች፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን ተመኝታለች።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በመልካም ስብእናቸውና በርሕራሔያቸው በመላው ኢትዮጵያ በታሪክ ሲታወሱ እንደሚኖሩም ገልጻለች።

Via የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት::

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...