አንዳንድ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ወንዝ እኔ ብቻ ልጠቀም የሚለው አቋማቸው እንደከሸፈ ሊገነዘቡ ይገባል

Date:

ታላቁ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን በመቀልበስ የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ቁልፍ የትብብር መሠረት መሆኑን  የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በሁለተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ ሀገሪቱ በውሃና ኢነርጂ ልማት ዘርፍ የምታከናውናቸው ተግባራት በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ አስተማማኝ የውሃ ፍሰት በመፍጠር ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንዳደረገ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የውሃ፣ የነፋስና የጸሐይ የኃይል አቅርቦት ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመቀነስ በቀጣናው አስተማማኝ የሆነ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን እየፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከጥቅምት 17 – 21 ባሉት ቀናት በሚካሄደው 2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ወቅት ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ባከናወነችው የትብብር ተግባራት ዙሪያ የማስገንዘብ ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ 10,000 የአሜሪካ ዶላር ተበረከተለት

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የሁልጊዜ ደጋፊ ዩስትሬት ፓርኪንግ (UStreet parking)...

ዶክተር ጌታቸው ተድላ ሁለት መፅሐፍትን ያስመርቃሉ

ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በዶክተር ጌታቸው ተድላ አበበ...