የእስራኤል ጦር በኻንዩኒስ በፈፀማቸው የአየር ጥቃቶች አካባቢውም በፍርስራሽ ክምር ተሞልቷል  

Date:

 

በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉ የቅርብ ጊዜ ክንውኖች፦

🔸 በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የኻን ዩኒስ ምስራቃዊ ክፍል ትናትና ጠዋት በእስራኤል የአየር ጥቃት እንደተፈፀመበት የፍልስጤም መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

🔸 ሁኔታው አስቸኳይ ቢሆንም እስራኤል የመድኃኒትና የሕክምና አቅርቦቶችን እንዲገባ መከልከሏን ቀጥላለች ሲሉ የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ገልፀዋል።

🔸 የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ሙሐመድ አቡ ሰልሚያ እንደተናገሩት፤፣ ሁለት ሺህ ሕፃናትን ጨምሮ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ እጅና እግራቸውን ያጡ ሰዎች አፋጣኝ የሰው ሠራሽ አካላት ሕክምና ያስፈልጋቸዋል።

🔸 የማዘጋጃ ቤቱ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ወደ 260 ሺህ ቶን የሚጠጋ ፍርስራሽ (ቆሻሻ) በጋዛ ጎዳናዎች እና የቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ላይ ተከምሯል።

🔸 የአካባቢው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የመስከረም 30 የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በእስራኤል የጥቃት እርምጃ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ 226 ሰዎች ተገድለው 594 ቆስለዋል።

🔸 ቅዳሜ ዕለት የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ አባላት ኢስታንቡል ውስጥ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳንን የተገናኙ  ሲሆን፣ በጋዛ የተኩስ አቁም ሁኔታ እና አስቸኳይ ሰብአዊ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...