በአርሲ ዞን አራት ወረዳዎች የተከሰተዉን የሚያጣራ የልዑካን ቡድን የማጣራት ሥራ ተጀመረ

Date:

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ (የኢሃተጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት እንዲሁም በሌሎችም የሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች እና ምዕምናን ላይ ግድያ እና ስቃይ መከሰቱን የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን መነሻ በማድረግ ጉዳዩን ከመሰረቱ የሚያጣራ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች የተካተቱበት አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ የተከሰተውን ችግር በአካል ለማጣራት ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ቦታዎች በመጓዝ ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡


የልዑካን ቡድኑ የማጣራት ሥራውን ጨርሶ የመጨረሻ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በጉዳዩ ላይ በጉባኤችን በኩል ይፋዊ መግለጫ እና ማብራርያ የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በትእግስት የማጠቃለያ ሪፖርቱን እንዲጠብቅ ጉባኤችን በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ አካላት ኃላፊነት በጎደለው መልክ ከግምት እና ካልተሟላ መረጃ በመነሳት በማሕበራዊ ሚዲያ ጉዳዩን አስመልክተው መረጃዎች መስጠታቸውን ተመልክተናል፡፡


ይህ ተግባር የማጣራቱን ሂደት የሚጎዳ እና አንዳንድ አካላትን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ሊወስድ የሚችል ተግባር በመሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ የምታሰራጩ አካላት በሙሉ ከፍ ያለ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ጉባኤችን አበክሮት ያሳስባል፡፡

ፈጣሪኢትዮጵያንይባርክ! ሕዝቧንም_ይጠብቅ!

  • የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...