የቱርክ ዕቃ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

Date:

የቱርክ አየር ኃይል ንብረት የሆነው C-130 ዕቃ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላን ከአዘርባጃን ተነስቶ ወደ ቱርክ በረራ በሚያደርግበት ወቅት ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶኻን በወቅቱ የአውሮፕላኑን ፍርስራሾች የማስመለስ እና የአደጋውን ምክንያት የማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነም ገልጸው ነበር።

በዚህም ቱርክ C-130 ዕቃ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላኖቿን ሙሉ በሙሉ ከበረራ ማገዷን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከአደጋው በኋላ ሌሎች C¬-130 አውሮፕላኖች የቴክኒክ ምርመራ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በውስጡ የሰው ኃይል እና የአውሮፕላን ጥገና አቅርቦቶችን ጭኖ ከምዕራብ አዘርባጃን በመነሳት ወደ ምስራቅ ጆርጂያ ከተሻገረ ብዙም ሳይቆይ የወደቀው አውሮፕላን፤ የአደጋ መንስኤው እስካሁን አልታወቀም።

የአደጋውን መንስኤ የሚያጣራ የምርመራ ቡድን የሚደርስበት ውጤት እንደሚገለጽ ያመለከተው ሚኒስቴሩ፤ መርማሪዎቹ ወደ አንካራ የመጡ የበረራ መረጃ እና የድምጽ መቅረጫዎችን በመመርመር ላይ መሆናቸውን አብራርቷል።

የወታደራዊ አውሮፕላኖች ዝርዝር የቴክኒክ እና የደህንነት ፍተሻዎችን አድርገው ካጠናቀቁ በኋላ እንደሚመለሱም ሚኒስቴሩ በመግለጫ ጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ 4 ሚሊዮን ገበሬዎችን በዲጂታል ለመመዝገብ አቅዳለች

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ አራት ሚሊዮን ገበሬዎችን በአገር...

ሕገ-ወጥና ጊዜያቸው ያለፈ ምርቶችን ሲሸጡ በተገኙ 52 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሕብረተሰቡን ጤናና ደኅንነት ለመጠበቅ...

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...