በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ30ሺ እስከ50ሺ የሚሆኑ ህጻናት ከስፓይና ቢፊዳ በሽታ ጋር ይወለዳሉ

Date:

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ30,000- 50,000 የሚሆኑ ህጻናት ከስፓይና ቢፊዳ በሽታ ጋር እንደሚወለዱና በዚህም ምክንያት እነዚህ ሕጻናት ለዕጽሜ ልክ የአካል ጉዳት ብሎም ለሞት ተጋላጭ እንደሚሆኑ ሆኘ ኤስ.ቢ.ኤች (HOPE-SBH) የተሰኘ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ጽርጅት አለም አቀፍ የስፓይና ቢፊዳና ሃይድሮሴፋለስ ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብር ላይ ተገልጿል።

ስፓይና ቢፊዳ ማለት ከነርቭ ዘንግ የዓፈጣጠር ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት/ክፍተት ነው። በአብዛኛው ጊዜ ስፓይና ቢፊዳ ያስባቸው ሕጻናት ፈሳሽ በአንጎላቸው ውስጥ ስለሚከማች ሃይድሮሴፋለስም ያጋጥማቸዋል።

ሃይድሮሴፋለስ የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት ሲሆን ይህም የአዕምሮ ግፊት እንዲጨምርና የራስ ቅል ላይ መለጠጥን ሊያስከትል ይችላል።

እስከ 70% የሚሆኑትን የስፓይና ቢፊዳ ችግሮች በበቂ ፎሊክ አሲድ መከላከል እንደሚቻል የተገለፀ ሲሆን የስፓይና ቢፊዳ ችግር በዋነኝነት በእናቶች የፎሊክ አሲጽ አጥረት (እስከ 70 %የሚሆነው) ፣ ባሉባቸው ተጓዳኝ የጤና ችግሮች እና በሚጠቀሟቸው አንዳንድ መድኃኒቶች ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ ተብሏል።

አንዲት ሴት እድሜዋ ከ 15–49 በሚሆንበት ጊዜ በተፈጥሮ ፎሊክ አሲድ የያዙ ምግቦችን አዘውትራ መመገብ እንዲሁም እርግዝናን በማቀድ ከእርግዝና በፊት ለሶስት ወራትና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብሎች በመውሰድ አና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ የስንዴ ዱቄት አና በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ዘይት በመጠቀም በሽታውን መከላከል እንደሚቻል ተነግሯል።

ሆኘ ኤስ.ቢ.ኤች በሽታው በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ እንዲሁም በችግሩ የተጠቁ ህጻናት እና ቤተሰቦች ህክምና እና እንክብካቤ አንዲያገኙ ማድረግን አላማው አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

ድርጅቱ በአሁን ሰዓት ከ5,700 በላይ ቤተሰቦችን ከሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለቀዶ ህክምና አገልግሎት ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡ ህጻናት እና ቤተሰቦች ማቆያ ቦታ በማዘጋጀት፣ በቅድመ እና ድህረ ቀዶ ህክምና ወቅት የመጠበቂያ እና ማገገሚያ ስፍራ ማዘጋጀት ለችግሩ ተጠቂ ለሆኑ ህጻናት ሽንትና ሰገራ እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ስልጠና በመስጠት የህጻናትን ጤና እንዲሻሻል እንደሚሰራ ተገልፇል።

በተጨማሪ በዘውዲቱ ሆስፒታል በሳምንት አራት ጊዜ ለወላጆች ግንዛቤ በመፍጠር ህጻናት ተገቢ የቤት ውስጥ እንክብካቤ እንዲያገኙ እየሰራ እንደሆነም ተነግሯል።

ድርጅቱ  የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት ያለባቸው ህጻናት ላይ የሚሰራ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...