ብሔራዊ ባንክ 420 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መደበ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በታሪክ ከፍተኛ የተባለ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳለዉ ከማስታወቁ ጎን ለጎን፣ ለዚሁ የበጀት ዓመት ሶስተኛ ሩብ ዓመት የሚውል 420 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መመደቡን ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ይህን ውሳኔ የወሰነው በውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ግልጽና ተገማች አሠራርን ለማጠናከር ባለው ቁርጠኝነት መሠረት መሆኑን ገልጿል። ዓላማውም በውጭ ምንዛሪ ፍሰት ላይ መተንበይነትን ለማምጣትና በገበያው ውስጥ ያሉ ተዋናዮችን እምነት ለመገንባት ነው።

በብሔራዊ ባንክ ይፋ በተደረገው መርሐ ግብር መሠረት፣ የውጭ ምንዛሪ ጨረታው በየሁለት ሳምንቱ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

ይህን ተከትሎ የመጀመሪያዉ ጨረታ በታህሳስ 28 ቀን የሚጀምር ሲሆን፣ እስከ መጋቢት 8 ቀን ድረስ በስድስት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን በሦስተኛው ሩብ ዓመት ለእያንዳንዱ የሁለት ሳምንት ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር መቅረቡ ታውቋል።

ባንኩ ለኅዳርና ታህሳስ ወር (የሁለተኛው ሩብ ዓመት አካል) ለሚያካሂደው ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አሳዉቋል፣ ይህም በሁለት ቀናት ተከፍሎ 50 ሚሊዮን ዶላር በኅዳር 23 ቀን እና 50 ሚሊዮን ዶላር በታህሳስ 7 ቀን እንደሚካሄድ ካፒታል ጋዜጣ የተመለከተዉ መረጃው ያሳያል።

በአዲሱ በጀት ዓመት (ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም.) የተካሄደው የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ 150 ሚሊዮን ዶላር የቀረበ ሲሆን 28 ባንኮች ድልድል ማግኘት መቻላቸው ይታወሳል።

ከአንድ ወር ቆይታ በኃላ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 10ኛዉ ዙር የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ ደግሞ (150 ሚሊዮን ብር ቀርቦበት ነበር) አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148 ብር ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል።

የብሔራዊ ባንኩ ይህን አይነት መርሐ ግብር ይፋ ማድረግ፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ተጠቃሚዎች የወደፊት እቅዳቸውን በደንብ እንዲያዘጋጁና የግብይት አቅጣጫዎችን በቀላሉ እንዲገምቱ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...