የጉምሩክ ዋጋ አተማመን ዘዴዎች

Date:


የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ የሚወሰነው በቅደም ተከተላቸው መሰረት በሚከተሉት 👉 ስድስት ዘዴዎች አማካኝነት ነው

   ✳️ የግብይት ዋጋ አተማመን ዘዴ

የግብይት ዋጋ ተደርጎ የሚወሰደው ወደ ኢትዮጵያ እንዲላክ ለተሸጠው ዕቃ በትክክል የተከፈለው ወይም የሚከፈለው የግብይት ዋጋ ሲሆን በጉምሩክ አዋጅና በመመሪያ የተመለከቱት ተጨማሪ ክፍያዎች ታክለውበት ነው፡፡

    ✳️. የአንድ አይነት ዕቃዎች ዋጋ አወሳሰን ዘዴ

የዕቃውን ዋጋ በግብይት ዋጋ አተማመን ዘዴ መወሰን ካልተቻለ ዕቃው ከመግባቱ በፊት በነበሩት 90 ቀናት ውስጥ በተመሳሳይ የንግድ ደረጃ እና በተቀራራቢ ብዛት ወደ ሀገር ገብተው በነበሩ ግንኙነት ለሌላቸው ገዢዎች የተሸጡ አንድ ዓይነት ዕቃዎች አስመልክቶ ዲክላራስዮን አቅራቢው በሚያቀርበው የዋጋ መረጃ በመነሳት የዋጋ ውሳኔ ይተላለፋል፡፡

   ✳️ የተመሳሳይ ዕቃዎች ዋጋ አወሳሰን ዘዴ

የዕቃውን ዋጋ ከላይ በተገለጹት ሁለት የዋጋ አተማመን ዘዴዎች መወሰን ካልተቻለ በ90 ቀናት ውስጥ በተመሳሳይ የንግድ ደረጃ እና በተቀራራቢ ብዛት ወደ ሀገር ገብተው በነበሩ ግንኙነት ለሌላቸው ገዢዎች የተሸጡ ተመሣሣይ ዕቃዎችን አስመልክቶ ዲክላራስዮን አቅራቢው በሚያቀርበው የዋጋ መረጃ መሰረት የዋጋ ውሳኔ ይተላለፋል፡፡

    ✳️ ወደ ኋላ የማስላት ዘዴ ዋጋ አወሳሰን

የዕቃው ዋጋ ከላይ በተገለጹት ሦስት የዋጋ አተማመን ዘዴዎች መወሰን ያልተቻለ እንደሆን  ወደ  ሀገር  ውስጥ  ከገባ  90  ቀናት  ያልበለጠው አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ ዕቃ በከፍተኛ ብዛት በሀገር ውስጥ በተሸጠበት ነጠላ ዋጋ  ላይ  በመመሥረት  ከዋጋው ላይ በመቀነስ ይወሰናል::

    ✳️ በወጪ ስሌት ላይ የተመሰረተ ዋጋ

ከላይ በተገለጹት አራት የዋጋ መተመኛ ዘዴዎች ዋጋ ሊወሰን በማይቻልበት ጊዜ ዕቃውን ለማምረትና ለመሸጥ የወጡ ወጪዎችን በሚያካትት ስሌት ላይ ተመሥርቶ ይወሰናል፡፡

   ✳️ ሚዛናዊ ዘዴን በመጠቀም ዋጋ መወሰን

ከላይ በተገለጹት አምስት የዋጋ መተመኛ ዘዴዎች ዋጋ ለመወሰን ካልተቻለ ከላይ የተጠቀሱትን የዋጋ ትመና ዘዴዎችን በቅደም ተከተላቸው አተረጓጎማቸውን በማስፋት ከጉምሩክ አዋጅ ድንጋጌዎች አጠቃላይ መርህ ጋር የተጣጣመ ሚዛናዊ ዘዴን በመጠቀም ይወሰናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...