43ኛ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን ያስተናገደው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል

Date:

አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እስካሁን 43 ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት አስተናግዷል፡፡

የማዕከሉ የገበያና ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ገበያው ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ማዕከሉ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

ትላልቅ ጉባዔዎችንና ሌሎች ሁነቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስተናገድ የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የጉባዔ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት ባህል ባንጸባረቀ መልኩ ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እስካሁን ድረስም 43 ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት ማስተናገድ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ማዕከሉ ትላልቅ ጉባዔዎችን፣ ኤግዚቢሽኖችን፣ የንግድ ውይይቶችን፣ ባህላዊ ክዋኔዎችንና ሌሎች ሁነቶችን ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ ሁሌም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

ማዕከሉ የተለያዩ ሁነቶችን ከሚያዘጋጁ አካላት በፈረንጆቹ እስከ 2028 ድረስ ጥያቄዎችን ማስተናገድ መጀመሩን አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም ጉባዔዎችንና ሌሎች ኹነቶችን የሚያዘጋጁ አካላት የኹነት ካሌንደር ቅድሚያ መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...