ኢትዮጵያ በጋዛ ለታቀደው ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችን እንድታዋጣ ጥያቄ ቀረበ

Date:

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በጋዛ ለታቀደው ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል ወታደሮቿን እንድታዋጣ እንዲያስቡበት መጠየቃቸውን ‘ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል’ የምዕራባውያን ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ዋሽንግተን በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ20 ነጥብ የጋዛ እቅድ ስር የተመለከተውን ዓለም አቀፍ ኃይል ለማዋቀር በሚደረገው ጥረት፣ ጥያቄው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።

እቅዱ በጦርነት ምክንያት ክፉኛ በፈራረሰው የፍልስጤም ግዛት ውስጥ፣ መልሶ ግንባታ እና ኢኮኖሚያዊ ማገገም ላይ ትኩረት ለሚያደርገው የሽግግር ወቅት ክትትል የሚሰጥ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል እንዲኖር ይጠይቃል። ግዛቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል።

ብዙ አገራት በዓለምአቀፍ ኃይሉ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግን በጥንቃቄ እየተመለከቱት መሆኑ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጸጥታ ኃይሉ ድጋፍ ለማግኘት ተግዳሮት እንዲገጥማት ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል።

በተለይም የተልዕኮው ዓላማ በጋዛ የሚንቀሳቀሰውን ሐማስን ትጥቅ ማስፈታት መሆኑ፣ አገራቱ ለመሳተፍ እንዲሰጉ አድርጓቸዋል ተብሏል። ይህ ስጋት በዕቅድ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የጸጥታ ኃይል አባላት የማሟላት ጥረትን እንዳወሳሰበው ተመላክቷል።

የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥትም በኩል ሆነ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።

በቅርቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት ባልተለመደ ሁኔታ ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች አለማንሳታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገለጻ ከሆነ፣ ውይይቱ ያተኮረው ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ “ለቀጣናዊ መረጋጋት እና በአፍሪካ ቀንድ ለሰላም መሠረት ለመጣል ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት” ላይ ብቻ ነበር።

አዲስ ስታንዳርድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...