በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል 236 ትምህርት ቤቶች ሁሉም ተማሪዎች አላለፉም

Date:

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
‎
‎የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ እንደገለጹት፣ የዘንድሮው ማለፊያ ነጥብ ለሁለቱም ክፍሎች ክልላዊ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን፣ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ደግሞ 48 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።
‎
‎​በዚህም መሠረት በ8ኛ ክፍል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት 86 ሺህ 502 ተማሪዎች መካከል 78 ሺህ 203 የሚሆኑት ተፈትነው 47 ሺህ 307 ተማሪዎች ማለፊያ ነጥቡን በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል።
‎
‎ይህም የክልሉን አጠቃላይ የማለፍ ምጣኔ 60.4 በመቶ የሚያደርሰው ሲሆን፣ ከአምናው የ63 በመቶ ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ3 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
‎
‎በተቃራኒው በ6ኛ ክፍል ከተፈተኑት 110 ሺህ 566 ተማሪዎች ውስጥ 70 ሺህ 584ቱ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት ያለፉ ሲሆን፣ የክልሉ የማለፍ ምጣኔ 63.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ውጤት ከአምናው የ56 በመቶ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት የታየበት ነው።
‎
‎​ከትምህርት ቤቶች አፈፃፀም አኳያም በ8ኛ ክፍል 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ ሲችሉ፣ 155 ትምህርት ቤቶች ግን አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
‎
‎በ6ኛ ክፍል ደግሞ 476 ትምህርት ቤቶች 100 በመቶ የማሳለፍ ስኬት ሲያስመዘግቡ፣ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል።
‎
‎የክልል ትምህርት ቢሮ
‎

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...