በኦሮሚያ ክልል የደገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተገደሉ

Date:

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት እሁድ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም. በፈጸሙት ጥቃት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ተፈራ ደሴ መገደላቸውን ምንጮች ተናገሩ።

በጥቃቱ በወረዳው የምትገኘው አኖ ቀሬ ቀበሌ ሊቀ መንበር አስፋወሰን ኃይሌን ጨምሮ ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል።

የዞኑ የፀጥታ መዋቅር ምንጮች ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ እንደተናገሩት፣ ዋና አስተዳዳሪው የተገደሉት እሁድ ከሰዓት በኋላ ሲሆን ጥቃት የተፈጸመው በደገም ወረዳ አኖ ቀሬ ቀበሌ ውስጥ ነው።

በዕለቱ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ምንጮቹ አስረድተዋል። የቀበሌ ሊቀ መንበሩን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው ምንጮች፣ በመንግሥት ባለሥልጣናቱ ላይ ለተከፈተው ጥቃት ተጠያቂ ያደረጉት በክልሉ የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ታጣቂዎችን ነው። ታጣቂ ቡድኑ እስካሁን ስለ ጥቃቱ መረጃ ያለው ነገር የለም።

የደገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የአቶ ተፈራን መገደል በተመለከተ ከክልሉ መንግሥትም ይሁን ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የተሰጠ አስተያየት የለም። ቢቢሲ ከዞኑ ዋና አስተዳደሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ባለልጣናትን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም።

በየካቲት 2017 ዓ.ም. ሱሉልታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አበበ ወርቁ በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል።

መንግሥት በሽብር ቡድንነት የፈረጀው እና ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በወቅቱ በወጣው መግለጫው ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።

በዚያው ዓመት ታኅሣሥ ላይ ደግሞ የዞኑ የውሃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስዩም አበራ፣ የዞኑ አደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን እጄታ እና የዞኑ የፋይናንስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ግዛው ተገድለዋል።

ጥቅምት ላይ በተመሳሳይ የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ከ45 በላይ ሰዎች የሚሆኑ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረው ነበር።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 7 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር ያለን ቁርኝት እጅግ...

‹‹ከኢትዮጵያዊ ባሕል ወደ አህጉራዊ ባሕል የተሸጋገርኩ ይመስለኛል››

‹‹ሀገርና የውርስ ቤትም አንድ ናቸው››     ጠበቃ መሠረት ሥዩም ...

በሆርሙዝ አቅራቢያ ሁለት መርከቦች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ መስመጣቸው ተነገረ

የባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ባለፉት አስር ቀናት በወሽመጡ ላይ...