የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 27ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሂድ ነው

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 125 ሚሊዮን ዶላር መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ረቡዕ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድ አስታውቋል።

ባንኩ ይህንን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የሚያካሄደው  ቀናት በፊት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ካካሄደው 500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በኋላ ነው።

ማዕከላዊ ባንኩ በወቅቱ ባካሄደው የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ ልዩ ጨረታ ከንግድ ባንኮች የ710 ሚሊዮን ዶላር ከፍተኛ ፍላጎት የቀረበ ሲሆን፤ ከተሳተፉት 22 ንግድ ባንኮች ውስጥ 21ዱ የዶላር ድልድል ማግኘት ችለዋል።

በዕለቱም ባንኩ ባከናወነው በዚህ ጨረታው የአንድ ዶላር አማካኝ ዋጋ 160.21 ብር ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። ይህም ከቀድሞው መደበኛ ጨረታ ጋር ሲነጻጸር የብር የመግዛት አቅም በአንድ በመቶ ገደማ ከዶላር አንፃር እንዲጠናከር አስችሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 7 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር ያለን ቁርኝት እጅግ...

‹‹ከኢትዮጵያዊ ባሕል ወደ አህጉራዊ ባሕል የተሸጋገርኩ ይመስለኛል››

‹‹ሀገርና የውርስ ቤትም አንድ ናቸው››     ጠበቃ መሠረት ሥዩም ...

በሆርሙዝ አቅራቢያ ሁለት መርከቦች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ መስመጣቸው ተነገረ

የባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ባለፉት አስር ቀናት በወሽመጡ ላይ...