የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የግል የጤና ተቋማትና የፀጥታ አካላት ዓርማውን እንዳይጠቀሙ አሳሰበ

Date:

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የማኅበሩን ዓርማ ያላግባብ እየተጠቀሙ ነው ያላቸውን የግል የጤና ተቋማት እና የፀጥታ አካላት ማኅበረሰቡን እያሳሳቱ በመሆናቸው፣ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በተቋቋመበት አዋጅ የማኅበሩን ዓርማ ከተፈቀደለት አካል ውጪ መጠቀም ክልክል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም የማኅበሩን ዓርማ ያላግባብ የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸውንና ማኅበረሰቡም ይህ መረዳት እንዳለበት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ አበራ ሉሌሳ ተናግረዋል፡፡

የማኅበሩ አምቡላንሶች አገልግሎት የሚሰጡት በጥንቃቄና ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን፣ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፖች ያመላልሳሉ መባሉ የተሳሳተ መረጃ እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ አብዛኛዎቹ አምቡላንሶች የማኅበሩ ቢሆኑም የመንግሥትና የግል ተቋማት አምቡላንስ የራሳቸው እንዳሏቸው ጠቁመው፣ አምቡላንስ በታየ ቁጥር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ነው መባሉ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡

‹‹የግል የጤና ተቋማት አምቡላንስ አላቸው፡፡ በአምቡላንሶቻቸው ላይ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሚል ጽሑፍ ባይኖርም፣ የማኅበሩን ዓርማ ለጥፈው ስለሚንቀሳቀሱ በኅብረተሰቡ ላይ ትልቅ ውዥንብር ነው የሚፈጥረው፤›› ሲሉም አስረድተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...