ለጥገና ሥራ በተለያዩ አካባቢዎች የነገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ይቋረጣል

Date:

ለጥገና ሥራ ሲባል ነገ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል

ከጠዋቱ 2:00 እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ ድንበሯ ሆስፒታል፣ ሱመያ መስጊድ፣ መገናኛ፣ ሾላ ገበያ፣ የካ ሚካኤል፣ ለም ሆቴል፣ መድኃኒያለም ትምህርት ቤት ጀርባ፣ መድኃኒያለም ኮንዶሚኒየም፣ ሩፋኤል፣ ፋይናንስ፣ ቦናት፣ ሸጎሌ ቴሌ፣ አንበሳ ጋራዥ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባና ውሃ ጋኑ አካባቢ (ጎማ አደባባይ) እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

በዚሁ ሰዓት አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ ቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ፣ አርሴማ ቤተ ክርስቲያን፣ ቃሊቲ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ቃሊቲ ገብርኤል፣ ቃሊቲ ማረሚያ ቤትና አካባቢው፤ እንዲሁም ኮተቤ ኮሌጅ፣ መሳለሚያ፣ ኮተቤ አማኑኤል ሆስፒታል፣ ዘርፌ ቦኖ፣ ፍናን ዳቦ፣ ቀርሳ ሚካኤል፣ ልደታ፣ ቢሪሞ ሜዳ፣ ሜክሲኮ ፌዴራል ፖሊስ፣ ጦር ኃይሎች ምድር ኃይል ግቢና ልደታ ፍርድ ቤት አካባቢዎችም አቅርቦቱ ይቋረጣል። መሳለሚያ፣ ሻንቅላ ወንዝ፣ ኳስ ሜዳ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ጋሽ መጋል፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋንና አካባቢውም በተመሳሳይ ጊዜ ከኃይል አቅርቦት ውጭ ይሆናሉ።

ከጠዋቱ 2:30 እስከ 8:30 ሰዓት ድረስ በሀዋሳ አቶቲ፣ አዲሱ ገበያና ወንዶ ማዞሪያ፤ በመቀሌ ደግሞ ኢትዮ ሼዊት ብረት ፋብሪካ፣ ዘነብ ወርቅ፣ ታቦት ማደሪያ፣ ወይራ ሰፈርና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል። በተጨማሪም ቡራዩ መስጊድ አካባቢ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ፣ ጸርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን፣ ቡራዩ ወለጋ ሰፈር፣ ከታና አካባቢውም አቅርቦቱ ይቋረጣል።

ከጠዋቱ 4:00 እስከ 8:30 ሰዓት ድረስ በሐረር ዶዶታ፣ ኪሌ፣ ቢስዲሞ፣ ሐረር ውሃና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

ከጠዋቱ 12:00 እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ በአርባ ምንጭ ባናታ፣ ባላ፣ ኮይቤ፣ አላዝና አካባቢው አቅርቦቱ ይቋረጣል።

ከጠዋቱ 7:30 እስከ 9:30 ሰዓት ድረስ መካኒሳ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ ሀና ማርያም፣ ሰፈራ፣ አብነት፣ ኮካ፣ ተ/ኃይማኖት፣ ጭድ ተራ፣ ፔፕሲ ፋብሪካ፣ ሰባተኛ በከፊል፣ መርካቶና አካባቢው፤ እንዲሁም ደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 04፣ 05፣ 06፣ አንኮበርና አካባቢው የኃይል አቅርቦት አይኖርም።

ከጠዋቱ 4:00 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ አቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት፣ ፓፍ ደም ሲኒማ፣ ሞኢንኮ ዱግዳ ኮንስትራክሽን፣ ሰላም ሕንፃ፣ ኪዳነ ምሕረት፣ ቃሊቲ 09፣ ቃሊቲ 08፣ ቃሊቲ መከላከያ ግቢ፣ አቃቂ ስታዲየም፣ ዮሐንስ ሆቴል፣ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጀርባ፣ ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ፣ አያት 49 ማዞሪያና አካባቢው ከኃይል አቅርቦት ውጭ ይሆናሉ።

በዚሁ የጊዜ ሰሌዳ ኮተቤ ኪዳነ ምሕረት፣ አንቆርጫ፣ ወሎ ሰፈር፣ ዳንሴ፣ ጫካ ፕሮጀክትና አካባቢው፤ በባህር ዳር ደግሞ ወገልሳ፣ ወንጀጣ፣ ጭምባና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የኃይል መቋረጡን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ የኃይል አቅራቢው አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ 4 ሚሊዮን ገበሬዎችን በዲጂታል ለመመዝገብ አቅዳለች

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ አራት ሚሊዮን ገበሬዎችን በአገር...