ኢትዮጵያ በካናዳ በተካሄደው 43ኛው የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የድርጅቱ ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።
በጉባኤው ላይ አባል ሀገራት በሰጡት ድምፅ መሠረት ኢትዮጵያ እና ቱርኪዬ እያንዳንዳቸው 133 ድምፅ በማግኘት የምክር ቤቱ አባል ሆነው መመረጥ ችለዋል።
በተመሳሳይም ኦማን 125 ድምፅ እንዲሁም ኢንዶኔዥያ 110 ድምፅ በማግኘት የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል።
