የአንጋፋ አለማየሁ ታደሰ የኪነጥበብ ምሽት!

Date:

የ66ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በትወና ጥበቡ የተመልካቾችን ልብ የገዛ፣ በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በፊልምና በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች የጥበብ አሻራውን ያሳረፈ፣ በአንድ የትወና ዘውግም ሆነ በአንድ ዓይነት ገጸ ባሕርይ ያልተገደበ፣ ከንጉሥ አጫዎች እስከ ንጉሥ የተለያዩ ገጸ ባሕርያትን በአስደናቂ ብቃት የተጫወተ፣ በእያንዳንዱ ገጸ ባሕርይ ውስጥ እንደልብ የሚገለጥ የኢትዮጵያ የትወና ጥበብ ደማቅ ኮከብ፣ አለማየሁ ታደሰ ነው!

🌟 ኮከብ ምሽት!

ኮከብ የሚወለደው እንዴት ነው?…

ከሐረር የልጅነት ትዝታዎቹ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጀመሪያ የትወና ሙከራዎቹ እስከ ታላላቅ የቴአትር መድረኮች፣ ከ”አንቲጎን” እስከ “ባቢሎን በሳሎን”፣ ከሬዲዮ እስከ የቴሌቪዥን ድራማ፣በአጠቃላይ የጥበብ ጉዞውን… 

ከዝናው ጀርባ ባሉ ትግሎቹ፣ ፈተናዎቹና ስኬቶቹ ዙሪያ እንወያያለን።

🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው!

ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል።

📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም

🕠 11:30 ሰዓት

📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ

🌟 አንድ ኮከብ፣ ብዙ ገጸ ባሕርያት!

🎭 አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዳኛው በአወዛጋቢ ውሳኔዎች ከሜዳ ተሰናበተ

በእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ 2 ውድድር ላይ የተካሄደ ጨዋታን ይመራ...

ሩሲያ ከሶቪየት ዘመን ወዲህ ከፍተኛውን የወታደራዊ በጀት አጸደቀች

ሩሲያ ከሶቪየት ህብረት ውድቀት ወዲህ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ የወታደራዊ...

ካይሮን በጭስ የሸፈነው ከባድ የእሳት አደጋ

በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በተከሰተ ከባድ የእሳት አደጋ ቢያንስ...

በፓርላማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡ ጥያቄዎችና ሀሳቦች

በ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ...