በሲዳማ የሕዝብ ማመላለሻ ላይ በደረሰዉ አደጋቨ 3 ሰዎች ሞቱ

Date:

በሲዳማ ክልል ከሀዋሳ ወደ በንሳ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ወረዳ ኦሎንሶ ሆሬ ቀበሌ ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር መለሠ ቡኑራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-02166 የሆነው ኤፍኤስአር የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በአደጋው ተገልብጦ የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ሲሆን፣ የተጎጂዎችን ቁጥር ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኢንስፔክተር መለሠ ጠቁመዋል።

የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እስካሁን ያልተለየ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም የመምሪያ ኃላፊው አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቀርጫንሼ ግሩፕና ጂሊ ሁለት ኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለገበያ አቀረቡ

ቀርጫንሼ ግሩፕ ከቻይናው የመኪና አምራች ጂሊ ጋር በመተባበር ሁለት...

ማንችስተር ዩናይትድ 4-0 ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብሬንትፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን 4-0 በማሸነፍ ድል...

የቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞች አገልግሎቱን ዲጂታል ሊያደርግ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞችን አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ በአጭር...

ከፈቃድ ውጭ የመማሪያ መጽሐፍትን ማተምና ለንግድ ማዋል ተከለከለ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ዝግጅት፣ ሕትመት፣ ስርጭትና...