ከፈቃድ ውጭ የመማሪያ መጽሐፍትን ማተምና ለንግድ ማዋል ተከለከለ

Date:

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ዝግጅት፣ ሕትመት፣ ስርጭትና አጠቃቀምን የሚመለከት አዲስ አስገዳጅ መመሪያ ቁጥር 1163/2019 ይፋ አድርጓል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተፈረመው መመሪያ፣ ከሚኒስቴሩ ወይም ከክልል ትምህርት ቢሮ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍትን ማተም፣ ማባዛትና ለንግድ ዓላማ ማዋልን ይከለክላል። መመሪያው በፌዴራልና በክልል የመንግሥት እና የግል ትምህርት ተቋማት፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

በመመሪያው መሠረት ተማሪ የተረከበውን መጽሐፍ ቢያጣ ወይም ለመማር በማይችል ደረጃ ቢያበላሽ፣ ተመሳሳይ ይዘትና ጥራት ያለው መጽሐፍ በምትክ ማቅረብ ወይም የመጽሐፉን የገበያ ዋጋ ከ20 በመቶ አስተዳደራዊ ቅጣት ጋር መክፈል ይጠበቅበታል። ይህንን ክፍያ ሳይፈጽም ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለመዛወር ከፈለገም የዝውውር ሰነድ እንደማይሰጠው ተደንግጓል።

መመሪያው የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት መደበኛ የአገልግሎት ዘመናቸው ቢያንስ ሦስት የትምህርት ዘመናት እንዲሆን ያዘጋጃል። በትምህርት ቤቶች አስተዳደራዊ ቸልተኝነት ወይም አግባብ ባልሆነ አያያዝ መጽሐፍት ከዚህ የአገልግሎት ዘመን በፊት ከጥቅም ውጭ ከሆኑ ተገቢው አስተዳደራዊና ሕጋዊ ተጠያቂነት እንደሚኖር አስጠንቅቋል።

ትምህርት ቤቶች መጽሐፍትን ለተማሪዎች በውልና በፊርማ ማስረከብ እና በዓመቱ መጨረሻ መሰብሰብ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ ወላጆችም ልጆቻቸው መጽሐፍትን በአግባቡ መያዛቸውንና መመለሳቸውን የመከታተል ግዴታ አለባቸው። ለመደበኛ ትምህርት የመጽሐፍና የተማሪ ጥመርታ 1 ለ1 እንዲሆንም መመሪያው ያስገድዳል።

ሚኒስቴሩ ከታተሙ መጽሐፍት ጎን ለጎን የተረጋገጡ የመማሪያ መጽሐፍትን በዲጂታል ፎርማት (PDF/e-Book) በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ለሕዝብ ክፍት እንደሚያደርግ ገልጿል። በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በነጻ እንዲሰራጩ የታተሙ መጽሐፍትን በገበያ ላይ መሸጥ ወይም ከፈቃድ ውጭ ማባዛትና ዲጂታል ቅጂዎቻቸውን ለንግድ ዓላማ ማዋል በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑም ተጠቅሷል።

ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍ አዘጋጆች ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪና የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ እንዲኖራቸው መመሪያው ይጠይቃል። ከተቀመጠው የወረቀትና የጥረዛ ስታንዳርድ ውጭ የታተሙ መጽሐፍትም በሕትመት ድርጅቱ ወጪ እንዲደገሙ ይደነግጋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ማንችስተር ዩናይትድ 4-0 ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብሬንትፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን 4-0 በማሸነፍ ድል...

የቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞች አገልግሎቱን ዲጂታል ሊያደርግ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞችን አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ በአጭር...

በሲዳማ የሕዝብ ማመላለሻ ላይ በደረሰዉ አደጋቨ 3 ሰዎች ሞቱ

በሲዳማ ክልል ከሀዋሳ ወደ በንሳ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ...

መቻል አትሌቲክስ ክለብ ሶስት ዋንጫዎችን አሸነፈ

6ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በአዲስ...