መንገዶች ነገ በአዲስ አበባ ይዘጋሉ

Date:

ነገ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ/ም በ ” ኢትዮጵያ ታምርት ” የ10 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የውድድሩ መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን ለገሃር መብራት፣ ቡናና ሻይ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ሳር ቤት (ፑሽኪን አደባባይ) ፣ ቄራ አዲሱ መሿለኪያ ድልድይ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ግሎባል ሆቴል፣ መስከረም ማዞሪያ ፣ ጥላሁን አደባባይ፣ ሳንጆሴፍ መብራት አድርጎ መስቀል አደባባይ ያበቃል።

በዚህም መሠረት:-

👉 ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ)
👉ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደቤይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
👉ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
👉ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት
👉 ከሠንጋ ተራ  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
👉 ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
👉ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
👉ከልደታ ፀበል ወደ አፍሪካ ህብረት መብራት
👉 ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
👉 ከቫቲካን ወደ ሳርቤት አደባባይ
👉ከቄራ አልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ መብራት
👉ከጎፋ ገብርኤል አቅጣጫ ወደ ጎፋ መስቀለኛ በስር
👉 ከዮሴፍ  ወደ ጎተራ ማሳለጫ
👉ከመስቀል ፍላዎር ወደ አጎና መስቀለኛ
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ በቅሎ ቤት ድልድይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በተጠቀሱት መስመሮች ከዛሬ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት 12፡00 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድም ፈጽሞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...