የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲስ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት መረጠች። አዲሱ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሮበርት ፕሬቮስት ሲሆኑ 69 ዓመታቸው ነው።
ቤተ-ክርስቲያኒቱን ሲመሩ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሊዎ 14ኛ ተብለው ይጠራሉ።
ሮበርት ፕሬቮስት የመጀመሪያው አሜሪካዊ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሆነዋል። ለበርካታ ዓመታት በፔሩ የኖሩ ናቸው። ማንነታቸው ይፋ ከመደረጉ በፊት በቫቲካን ጭስ ማውጫ አዲስ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት የመመረጡ ምልክት የሆነው ነጭ ጭስ ታይቷል። በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡ ምዕምናን እና ታዳሚዎች በሆታ መልዕክቱን ተቀብለዋል።
