ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን “ፈሪዎች” ሲሉ ወቀሱ

Date:

የትራምፕ አስተዳደር መድልዎ ደርሶባቸዋል ብሎ የጥገኝነት መብት የሰጣቸው ‘አፍሪካነሮች’ ባለፈው ሰኞ  አሜሪካ  ገብተዋል።

መድልዎ ደርሶባቸዋል መድልዎ ደርሶባቸዋል ሚለውን ክስ ውድቅ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎስ፤ የሸሹት በአፓርታይድ ዘመን ያልነበረውን እኩልነት ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ስላልተመቻቸው ነው ብለዋል።

“እኛ ደቡብ አፍሪካውያን ጠንካሮች ነን። ከችግሮቻችን አንሸሽም። እዚህ ሆነን ችግሮቻችንን እንፈታለን። መሸሽ የፈሪ ነው፤ የወሰዳችሁት እርምጃ  የፈሪ ነው” ሲሉ ወቀሰዋል።

ራማፎሳ፤ ዶናልድ ትራምፕና ኤለን መስክ በነጭ ገበሬዎች ላይ “ዘር ማጥፋት” ተፈፅሟል በማለት ላቀረቡት ክስ፣ በአቢጃን በተካሄደው የአፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም ላይ በሰጡት ምላሽ፤ “በአህጉሪቱ ውስጥ ቅኝ ገዥዎች መጥተው የቆዩባት ብቸኛ ሀገር የኛ ናት፤ ከሀገራችን በጭራሽ አላባረርናቸውም።” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሄዱት ሰዎች የስደተኝነት መስፈርቶችን እንደማያሟሉ አጽንኦት በመስጠት፤ በቅርቡ ከትራምፕ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ጉዳዩን በቀጥታ እንደሚያነሱ ተናግረዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...