በዓመት ከ7,000 በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ኤድስ የሚያዙ ሲሆን አስር ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ይሞታሉ የተባለ

Date:

የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ ሆኖ የታየው በቀን ሰራተኞች በተማሪዎች እና በአጠቃላይ በማህበረሰብ ውስጥ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ ከአንድ በመቶ በታች ነው ሲባል ዝቅተኛ ቢመስልም አሁን ባለበት ካልተገታ በድጋሚ ወረርሽኝ የሚሆንበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ለበሽታ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱ ወረርሽኝ የመሆን እድሉን ሊያሰፋው ይችላል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡

በዚህም ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንዳለ እንደሚገመትም ተናግረዋል፡፡

የስርጭት መጠኑ ከክልል ክልል ይለያያል ያሉት ስራ አስፈፃሚው አዲስ አበባ መጠኑ ከፍተኛ ሆኖ ከሚታይባቸው መካከል ቀዳሚ እንደሆነችም ያስረዳሉ፡፡

ጋምቤላ፣  ሀረሪ፣ ትግራይና አማራ ክልል ከፍተኛ ስርጭት የሚታይባቸው ከተሞች ናቸው ተብሏል።

እድሜአቸው ከ15 እስከ 29 ዓመት ያሉት ወጣቶች እና ሴቶች አዲስ የመያዝ እድላቸው 70 በመቶ ነው ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...