የስፔስኤክስ የህዋ ጉዞ ሙከራ ለምን ከሸፈ?

Date:



የኢሎ
ን መስክ የሕዋ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ስፔስኤክስ የሰውን ልጅ ወደማርስ የመውሰድ ምርምር አካል የሆነች “ስታርሺፕ” ሮኬት ለሙከራ ቢያመጥቅም፣ ከ30 ደቂቃ የአየር ላይ ቆይታ በኋላ መበታተኗ ታውቋል።

በስፔስኤክስ የሰውአልባ ሮኬት ላይ ተመሳሳይ አደጋ ሲያጋጥም የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

ከአሜሪካ ቴክሳስ የሕዋ ማምጠቂያ ጣቢያ  እንድትወነጨፍ ቢደረግም በነዳጅ ማከማቻዋ ላይ ያጋጠመው ፍሳሽ ለአደጋው ምክንያት መሆኑን ስፔስ ኤክስ አስታውቋል። 

ስፔስኤክስ በሰጠው መግለጫ “ስታርሺፕ ቅፅበታዊና ያልተጠበቀ የመበታተን አደጋ አጋጥሟታል፤ መረጃዎችን በመገምገም ለቀጣዩ ሙከራ የምናደርገው ጥረት ይቀጥላል” ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

የአሜሪካን የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በበኩሉ በሰጠው መግለጫ “በስፔስኤክስ ስታርሺፕ 9 ተልዕኮ ወቅት ችግር መከሰቱን አረጋግጦ፤ በሮኬቷ ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...