የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ማዕቀቡ ያለ ሀገሮቻቸው ፈቃድ ከለላ ያላቸውን ግለሰቦች ለፍርድ ለማቅረብ የሞከሩ 4 ዳኞች ላይ እንደሚጣል ገልጿል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አይሲሲ በመሠረተ ቢስ እና ፖለቲካዊ ክስ አሜሪካ እና የቅርብ ወዳጃችን እስራኤልን ዒላማ ማድረጉ ማብቃት አለበት” ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ጽፈዋል። አራቱም ዳኞች ሴቶች ናቸው።
አይሲሲ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ “ነጻነቱን ለመናድ የተደረገ ግልጽ ሙከራ” መሆኑን ገልጻል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
