በኢትዮጵያ ከሚገኙ 31 ባንኮች ውስጥ ሶስቱ ብቻ ሴት የቦርድ ሊቀመንበር አላቸው

Date:

በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉ በ2015 ሴቶች 14 በመቶ የቦርድ መቀመጫዎችን ይዘው የነበረ ሲሆን ባለፉት 10 አመታት በ5 በመቶ ተሻሽሎ አሁን ላይ የሴቶች ውክልና በ31 ባንኮች ወደ 19 በመቶ አድጓል።

በ10 አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክና አቢሲኒያ ባንክ ትልቅ ለውጥ ያመጡ ሲሆን ከ0% የሴቶች ውክልና ተነስተው በቅደም ተከተል ወደ 30%፣ 33% እና 10% አሳድገዋል።

ከሁሉም ባንኮች እናት ባንክ ከፍተኛውን የሴቶች የቦርድ ውክልና ሲያስመዘግብ የባንኩ 55 በመቶ የቦርድ አባላት ሴቶች ናቸው።

አሁን ላይ የኢትዮጵያ ባንኮች 10 በመቶ ቦርዳቸው በሴቶች ሲመራ ይህም ከዓለም አቀፉ የ8.4 በመቶ የተሻለ ነው።

ከባንኮቹ በሴት ቦርድ የሚመሩት እናት ባንክ፣ ዘመን ባንክ እና ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እንደሆኑ ሲመላከት አሁንም በቦርዱ ምንም ሴት ያላካተተ ባንክ ስለመኖሩ እና 12 ባንኮች ደግሞ 1 ሴት የቦርድ አባል ብቻ እንዳካተቱ ተገልጿል።

በ2024 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ በአንድ ባንክ ውስጥ ቢያንስ ሁለት ሴት የቦርድ አባላት መኖር አለባቸው ያለ ሲሆን የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ አሁንም ብዙ ስራ ይቀራል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢሆንም በድርጅቶች የአመራርነት ስፍራ ላይ አሁንም በብዛት የፆታ መመጣጠን እንደሌለ ጥናቶች ያሳያሉ።

በ2023 በሞርጋን ስቴንሊ የተሰራ ጥናት ብዝሃ ቦርድ ያላቸው ድርጅቶች ከሌላቸው አንፃር በፋይናንስ የተሻለ ውጤት እንደሚያመጡ ሲያሳይ ከፆታ አንፃር ሁለቱንም ያካተቱ ድርጅቶች አካታች ካልሆኑት ድርጅቶች የተሻለ ውጤታማም ይሆናሉ።

በ2024 ዴሎይት ባወጣው ሪፖርት በአለም ላይ ካሉ የቦርድ ስፍራዎች ውስጥ ሴቶች የያዙት 23.3 በመቶውን ብቻ ነው።

በተጨማሪ 8.4 በመቶ የሚሆኑት ቦርዶች ብቻ በሴት ሊቀመንበርነት ሲመሩ ከዋና ስራ አስፈፃሚዎች ውስጥ 6 በመቶዎቹ ብቻ ሴቶቸ ናቸው።

(መረጃው ከ APEX የሊንክዲን ገጽ የተገኘ ነው )

@TikvahEthMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...