የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሜሪካ በኢራን የኒውለክሌር ተቋማት ላይ ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ ሰጠ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ የፈጸመችውን ጥቃት “አደገኛ ማባባስ” ሲሉ የገለፁት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ “ይህ ግጭት በፍጥነት ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ የሚችልበት ስጋት እየጨመረ ነው፤በሰላማዊ ዜጎች፣ በአካባቢው እና በዓለም ላይ አስከፊ መዘዝ አለው” ብለዋል።
ዋና ፀኃፊው በኤክስ ልጥፋቸው ላይ “በዚህ አደገኛ ሰዓት ውስጥ የቀውስ ሽክርክሪትን ማስወገድ በጣም አስፈላጊ ነው። ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለም። ብቸኛው አማራች ዲፕሎማሲ ነው። ብቸኛው ተስፋ ሰላም ነው” ሲሉ አስፍረዋል።
