የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ኢራን በፈጸመችው ጥቃት 11 ሰዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታልመወሰዳቸውን ገልጿል።
ጉዳቱ ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አንድ የ30 ዓመት ሰው በፍንጥርጣሪዎች በላይኛው የሰውነት ክፍሉ ላይ ተመትቶ መካከለኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።
የተቀሩት 10 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የእስራኤል የአየር ኃይል በምዕራብ ኢራንበሚገኙ “ወታደራዊ ዒላማዎች” ላይ አዲስየጥቃት ዘመቻ መጀመሩ ተናግሯል።
ይህ የሆነው የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኢራንሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ከገለፀ በኋላ ነው።
የመከላከያ ኃይሉ አክሎም በኢራን ግዛት በሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል።
