ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተገለፀ

Date:


የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የንቅናቄ መድረክ በሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ25 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።

ይህም በወረርሽኙ ምክንያት በህጻናት ላይ የሚደርስ ጫናን ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል።

ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻውም በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰተው የፖሊዮ ወይም የልጅነት ልምሻን ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት 50 ዓመታት በተከናወኑ የክትባት ስራዎች  154 ሚሊየን ዜጎችን መታደግ መቻሉ በንቅናቄ መርሃግብሩ ተነስቷል።

እንዲሁም የህጻናትን የመኖር ዕድልን 40 በመቶ ለማሳደግ አስችሏል ነው የተባለው።

ሆኖም አሁን ላይ ዓለም አቀፍ ላይ ባለው ጫና ምክንያት ወረርሽኙ መከሰቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በእ.ኤ.አ በ2025  በተደረገ ምርመራ 41 ህጻናት በወረርሽኙ መጠቃታቸው ተነግሯል። ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻውም ከዚሁ ክስተት ጋር የተገናኘ ነው ተብሏል።

የልጅነት ልምሻ ችግርን ለመከላከል ክትባት በጤና ተቋማት ሲሰጥ መቆየቱ የተገለጸ ቢሆንም በኢትዮጵያ ከ638 ሺህ በላይ ከ5 ዓመት በታች የሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት አለመውሰዳቸውን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያነሳል።

የክትባት ዘመቻውም ከዚህ ቀደም ክትባት ያገኙትንም ያላገኙትንም የሚያጠቃል ነው ተብሏል።

ክትባቱ ቤት ለቤት የሚሰጥ እንደመሆኑ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ክትባቱ እንዳያመልጣቸው ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...