ሃይኒከን ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ሸገር ከተማ ኮዬ ፈጨ ክ/ከተማ በሚገኙ ቁጥራቸው ከ75 በላይ የሆኑ አባወራዎችን በወተት፣ በከብት እና በዶሮ እርባታና በመሳሰሉት የገቢ ማስገኛ ሥራዎች በማደራጀት ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታውቋል።
ሃይኒከን ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝ እና ግለሰቦችን በማሰልጠን ወደ ሥራ እያስገባ እንደሚገኝ ያስታወቀ ሲሆን፤ ከማህበረ ሕይወት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት እና ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የኮየ ፈጬ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክትን የኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች፣ የኮዬ ፈጨ ክፍለ ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት ርክክብ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ የዶሮ እርባታ፣ የከብት ማደለቢያ እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ሲሆን፤ ለ45 ሰው ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ነው የተባለው።
ፕሮጀክቱ 20 ሚለዮን ብር የተሰራ ሲሆን ከቂሊንጦ ፕሮጀክት ጋር አብሮ 33 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖበታል።
የሃይኒከን ኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ዊልያም እና የኩባንያው የሰስተነብሊቲ የውጭና የመንግሥት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር “ኘሮጀክቶቹ ኩባንያው ከኀብረተሰቡ ጋር አብሮ የማደግ አላማው አካል ናቸው” ብለዋል።
የማህበረ ህይወት ፎር ሶሻል ዴቨሎመንት ተወካይ እንደተናገሩት ከሄንከን ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ግንባታ በማከናወንና ለሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ለተጠቃሚዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ያደረገ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሁለት ወር በፊት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ሥራ የሚገኙትን ሁለት ቡድኖች ወደ ሥራ እንዲገቡ አስችሏል፡፡
ሃይኒከን ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ላደረጉት የኮዬ ፈጪ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ የወረዳ አስተዳደር አካላት እንዲሁም የማህበረ ህይወት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ምስጋና አቅርቧል።
