ለቡና ላኪነት የመነሻ ካፒታል በ 15 እጥፍ አድጎ ወደ 20 ሚሊዮን ብር ተሻገረ

Date:

በአዲሱ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር መመሪያ መሠረት፣ የቡና ላኪነት ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልገው የመነሻ ካፒታል በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ። ይህ ለውጥ ከዚህ በፊት በዘርፉ ላይ የነበሩ የንግድ ደንቦችን ለማጠናከርና በዘርፉ ያለውን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመቀነስ ታስቦ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

የግል አመልካቾች ከዚህ በፊት 1 ሚሊዮን ብር ያስፈልግ የነበረው የመነሻ ካፒታል፣በ 15 እጥፍ ጨምሮ አሁን ወደ 15 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሏል።

በተመሳሳይ መልኩ የአክሲዮን ማኅበርና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከዚህ ቀደም 1.5 ሚሊዮን ብር የነበረው የመነሻ ካፒታል፣ በአዲሱ መመሪያ ወደ 20 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሏል። ይህ የካፒታል ጭማሪ ደግሞ 13.3 እጥፍ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ይህንን ለውጥ ያመጣው “የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 1106/2017” በሚል አዲስ መመሪያ ነው።

የመመሪያው የቡና ላኪዎችን የድጋፍ፣ የክትትልና የቁጥጥር ስርአትን ማሟላት ፣ የመነሻ ካፒታልን ከወቅታዊ የቡና ግብይት ጋር ማጣጣም ፣ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቶችን በመጠቀም የሚፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶችን መከላከልና የመቆጣጠር ዓላማ እንዳለዉ ካፒታል ተመልክቷል።

በዚህ ሳምንት ተግባራዊ መደረግ የጀመረዉ ይህ አዲስ መመሪያ በቡና ላኪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በዘርፉ ላይ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ይሆናል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...