ሩሲያ እና ዩክሬን ዛሬ በኢስታንቡል የሚያደርጉት ውይይት ተጠባቂ ሆኗል

Date:

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ጦርነቱ እየጠነከረ ቢመጣም፤ ዓለም ዛሬ በኢስታንቡል የሚድረገውን የሁለቱን ሀገራት ውይይት ውጤት በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል።

በኢስታንቡል ከተማ ዛሬ ለሚደረገው የሰላም ድርድር የዩክሬን ተወካዮች የሰላም ስምምነት ረቂቅ ይፋ አድርገዋል።

ረቂቁም የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል የታጋቾች ልውውጥ እና የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች የፊት ለፊት ውይይት ትኩረት ካደረገባቸው ነጥች መካከል ይጠቀሳሉ።

በኢስታንቡል ዛሬ እንደሚደረግ የሚጠበቀው ውይይት ላይም ረቂቁ ይቀርባል የተባለ ሲሆን፤ በሞስኮ እና ኬቭ መካከል ለሶስት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም ይረዳል ተብሎለታል።

የዩክሬን ባለስልጣናትም ረቂቁን በኢስታንቡል ለውይይት ከመቀመጣቸው በፊት ለሩሲያ ተወያዮች መላካቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ነገር ግን ሩሲያና ዩክሬን የሰላም ስምምነቱን ቢፈፅሙም ሩሲያ ከዩክሬን ላይ በተወሰዱ ግዛቶች ላይ የሩሲያን ሉዓላዊነት እውቅና መስጠቷ በዩክሬን በኩል ቅቡልነት እንደማይኖረው ሮይተርስ በዘገባው አክሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶንላድ ትራምፕም ‘’ሞስኮና ኬቭ በሰላም ስምምነቱ ላይ በጋራ መስራት አለባቸው፤ ይህ ከሆነ ጦርነቱ የማይቆምበት ምክንያት የለም’’ ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...